Emmanuel Full Gospel Sermons

  • Author: Vários
  • Narrator: Vários
  • Publisher: Podcast
  • Duration: 4:48:37
  • More information

Informações:

Synopsis

Sermons from the pulpit of EFGBC

Episodes

  • እግዚአብሔርን ማወቅ (ዮሐ. 17፥3)

    31/08/2018 Duration: 23min

    ስለ እግዚአብሔር ማንነት ጠንቅቀው የማያውቁ ሰዎች "በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥረናል" የሚለውን ቃል ያለአግባብ ሲጠቀሙ እናያለን። ይህም ማለት ሰዎች እግዚአብሔር የቅዱሳን ጋር የማይካፈላቸው ባህሪዎች (Incommunicable Characters of God) እና ከቅዱሳን ጋር የሚካፈላቸው ባህሪዎች (Communicable characters of God) እንዳሉት አለመረዳታቸውን ያሳያል። በዚህ ትምህርት ላይ ፓስተር ፍቅሩ አጭርና ግልጽ በሆነ መንገድ የትኞቹን የእግዚአብርሔር ባህሪያት እንደምንካፈልና የትኞቹን እንደማንካፈል ከእግዚአብሔር ቃል ያሳዩናል። ይኼ ትምህርት ለሁሉም ክርስቲያን (በተለይ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ቅዱሳን ልዩነት ትክክለኛ ግንዛቤ ላላገኙ) ይጠቅማል። ሼር በማድረግ ላልሰሙ እናሰማ! በተረፈ በፌስ ቡክ እና በዌብሳይታችን ለመከታተል የምትፈልጉ ወገኖች በዚህ አድራሻችን https://www.facebook.com/efgbc1 efgbc.net ልታገኙን ትችላላችሁ! ጌታ ይባርካችሁ።

  • ከሽንፈት ነጻ ወጥተናል (ሮሜ 8:5-17)

    16/03/2018 Duration: 47min

    ፓስተር ፍቅሩ ሞሲሳ የሮሜ መጽሐፍ ትምህርት @Emmanuel Full Gospel Believers Church 2018

  • ከህግ ነጻ ወጥታችኋል (ሮሜ 7፡ 1-6)

    23/12/2017 Duration: 49min

    ሮሜ 7:1-6 1. ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? 2. ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች። 3. ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም። 4. እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ። 5. በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና፤ 6. አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም።

  • ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ 6፡ 12-23)

    20/12/2017 Duration: 45min

    ሮሜ 6፡ 12-23 ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚህ ምዕራፍ ላይ ሶስት መሰረታዊ ነገሮች ያሳየናል። እወቁ (ከክርስቶስ ጋር ለኃጢያት ሞተናል፥ ለእግዚአብሔር እንድኖርች ከክርስቶስ ጋር ተነስተናል) 2. ቁጠሩ (count yourselves) 3. አቅርቡ (present yourselves) (ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ)

  • እግዚአብሔር ይፈርዳል (ፓስተር ደሳለኝ ኢተፋ)

    07/12/2017 Duration: 35min

    ሉቃስ 18 1.ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ 2. እንዲህ ሲል። በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። 3. በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች። ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። 4. አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ። ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ 5. ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። 6. ጌታም አለ። ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። 7. እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? 8. እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

  • ለኃጢያት ሞታችኋል (ሮሜ 6:1-11)

    01/12/2017 Duration: 45min

    ሮሜ 6:1-11 1 እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም። 2 ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? 3 ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? 4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። 5 ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤ 6 ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና። 7- 8 ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤ 9 ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና። 10 መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል። 11 እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቈጠሩ።

  • በክርስቶስ ኢየሱስ የመጽደቃችን በረከቶች (ሮሜ 5:1-11)

    22/11/2017 Duration: 41min

    በክርስቶስ ኢየሱስ የመጽደቃችን በረከቶች ፓስተር ፍቅሩ ሞሲሳ አማኑኤል ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን 10.22.2017